ለኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ
የኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማኀበር የባለአክሲዮኖች 21ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እሁድ ታህሣሥ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ለማካሄድ ፕሮግራም ተይዞ የነበረ ቢሆንም በዕለቱ ምልአተ ጉባኤው ባለመሟላቱ ጉባኤው ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡ በዚህም መሰረት ጉባኤውን በድጋሚ መጥራት አስፈላጊ ስለሆነ 21ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እሑድ ጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በኔክሰስ(Swiss Inn) ሆቴል ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የማህበሩ ባለአክሲዮኖች በሙሉ በተጠቀሰው ቦታ ቀንና ሰዓት እንድትገኙ የዲሬክተሮች ቦርድ የአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ሀ. የባለአክሲዮኖች 21ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
- የጉባኤውን አጀንዳዎች ማፅደቅ፤
- የዲሬክተሮች ቦርድን እ.ኤ.አ የ2021/22 ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ
- የውጭ ኦዲተሮችን እ.ኤ.አ የ2021/22 የሂሳብ ዘመን ሪፖርት ማዳመጥ
- በዲሬክተሮች ቦርድ መደበኛ ሪፖርትና በኦዲት ሪፖርት ላይ ውይይትና ውሳኔ
- እ.ኤ.አቆጣጠር 2021/22 የባለአክሲዮኖች የትርፍ ክፍፍል ሁኔታ ቦርዱ በሚያቀርበው ሀሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን
- የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ የሥራ ዋጋና ወርሃዊ የአበል ክፍያ መወሰን
- የአገልግሎት ጊዜአቸውን ባጠናቀቁ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት ምትክ ምርጫ ማካሄድ
- የዕለቱን ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ማፅደቅ
ለ. የ2ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች - የጉባኤውን አጀንዳዎች ማፅደቅ፤
- የማህበሩን ካፒታል ማሳደግ፤
- በአዲሱ የንግድ ህግ መሰረት የተሻሻለውን የማህበሩን መመሥረቻ ጽሁፍ ማፅደቅ
- የዕለቱን ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ማፅደቅ
ማሳሰቢያ፡- በስብሰባው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች በንግድ ህጉ አንቀፅ 373 እና 377 መሠረት ጉባኤው ከሚካሄድበት 3 ቀን በፊት ገርጂ ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ አጠገብ ወይም ገርጂ ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የዋና መሥሪያ ቤቱ ጽ/ቤት መጥታችሁ የውክልና መስጫ ቅጽ በመሙላት መወከል የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በዚሁ መሠረት ስልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የውክልና ሥልጣን የተሰጣቸው ተወካዮችም በስብሰባው ላይ ባለአክሲዮኖችን ወክለው መገኘት እንደሚችሉ እናስታውቃለን፡፡ በስብሰባዉ ላይ ባለአክሲዮኖችም ሆናችሁ ህጋዊ ተወካዮች ማንነታችሁን የሚገልፅ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ይዛችሁ መገኘት ይጠበቅባችኋል፡፡
ኆኀተ-ጥበብ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ
ስልክ- 0116 29 89 83, 0912661100